ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2008)
የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በጋምቤላ በተደራጁ ሃይሎች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ አዲስ ነገር አይደለም ማለታቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘገበ።
“የምናውቀው ድርጊቱን የፈጸሙት እስከ ፍንጫቸው የታጠቁ፣ የተደራጁና የሚሰሩትን የሚያውቁ ናቸው። በዚህኛው የአፍሪካ ክፍል ጥቃቱ ያን ያክል የሚያስገርም አይደለም” ማለታቸውን ዋሽንግተን ፖስት በዘግባው አስፍሯል።
አቶ ጌታቸው ረዳ መንግስታቸው ከኢትዮ- ደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ በጥቃት አድራሾቹ ላይ የጋራ ጥቃት ለመክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
ኢትዮጵያውያን ሃዘናቸውን ለመግለፅና ለተጨፈጨፉት ወገኖች መንግስት መግለጫ ለቀናት ባለማውጣቱ የተሰማቸውን ንዴት በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሲገልጹ መዋላቸውን ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል።
የአርቡ ጥቃት ሰለባዎች በአብዛኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የኑዌር ጎሳ አባላት መሆናቸውን ጠቅሶ የዘገበው ዋሽንግተን ፖስት፣ በዚህ አመት በኑዌርና በአኝዋክ ጎሳዎች መካከል ደም ያፋሰሰ ግጭት ተከስቶ እንደነበርና ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስትም በቅርቡ ጊዜ የክልሉን ፖሊስ ትጥቅ ማስፈታቱ አሁን ለተፈጸመው የጅምላ ዕልቂት የራሱን አስተዋጽዖ አበርክቶ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።
የጋምቤላ ዕልቂት የተከሰተው በወሳኝ ሰዓት መሆኑን የዘገበው ዋሽንተን ፖስት፣ ጭፍጨፋው የተከሰተው በምስራቅና ሰሜን ኢትዮጵያ ከ10.2 ሚሊዮን ህዝብ በተራበበትና፣ በኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ በነበረውና እንደሰብዓዊ መብት ድርጅቾት ግምት ከ200 ሰዎች በላይ በተገደሉበት ወቅት መሆኑ ሁኔታውን አወሳስቦታል በማለት ዘግቧል።
ጥቅም እንደማያገኝም መመሪያ ተላልፏል። ከዚህ አዲስ መመሪያ ጋር በተያያዘ በሰራዊቱ ውስጥ የተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ሳያገኝ ይበልጡንም ቅሬታውን እያበረታ መቀጠሉን የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል።
በግልጽ በአዋጅ የተደነገገው መመሪያ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ እስከ 2000 ዓ.ም ሰራዊቱን የተቀላቀሉ ኮንትራታቸውን ስለጨረሱ የመሰናበት መብት ይኖራቸው እንደነበርም ተመልክቷል።