በጉንዶ መስቀል ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ ውጥረት ነግሷል

መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በጉንዶ መስቀል ከተማ በሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ1 200 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ መወሰኑን ተከትሎ በከተማው ውጥረት ነግሷል። የከተማው ባለስልጣናት ህዝቡን ሰብስበው ቤቶቻችሁን አፍርሱ ብለው ትእዛዝ ሲሰጡ፣ ነዋሪዎቹ ግን አጥብቀው ተቃውመዋል። መስከረም 13 ቀን በከተማው የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በፌደራል ፖሊሶች ቢጨናገፍም፣ ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለና የከተማው መስተዳድር ተጨማሪ ሃይል እንዲገባ መጠየቁን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
አንድ ነዋሪ ” ቦታው ለኢንቨስተር መሰጠቱን ገልጾ፣ መስተዳድሩ ቤቶችን ወደ ማፍረስ ከገባ ያለጥርጥር ግጭት ይነሳል ” ብሎአል።