በጅጅጋ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ መፈጠሩ ታወቀ

በጅጅጋ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ መፈጠሩ ታወቀ
(ኢሳት ዜና የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት የኦሮምያ ክልልና ህዝብ ማንኛውም አይነት የግብርና ውጤቶች ወደ ሶማሊ ክልል እንዳይገባ ማገዱን ተከትሎ፣ ጅጅጋ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝና ህዝቡም ለችግር እንደተዳረገ ተናግረዋል። አቶ አብዲ ሙሃመድ የሚመራው የክልሉ መንግስት ችግሩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ነዋሪወች ይናገራሉ።
የምግብና ሌሎችን ሸቀጦች እየተወደዱ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በተለይ በጫት እና ፍራፍሬ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ቤተሰቦች የችግሩ ዋነኛ ተጠቂዎች ሆነዋል። በከተማው ወትሮ የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ በመዳከሙ የሚበላ እየጠፋ ነው በማለት ነዋሪዎች ጭንቀታቸውን ገልጸዋል።