በጂንካ በተካሄደው ቤት የማፈራረስ ዘመቻ በርካታ ዜጎች መጠለያ አልባ ሆኑ

ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ አርኪሻ ቀበሌ ኬላ መንደር ነዋሪዎች ቤቶቻቸዉ በዶዘር እንዲፈርስ በመደረጉ ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸዉንና በእሪታና ለቅሶ መንገድ በመዝጋት ጥቅምት 25፣ 2008 ከሰዓት በኃላ በማሰማታቸዉ ልዩ ኃይልና ፖሊስ ለመበተን ሲሞክሩ ቦታ እየቀያየሩ ተቃውሞአቸውን እስከ ምሽት ሲያሰሙ ቆይተዋል።
ጥቅምት 27ትም እንዲሁ ቤት ማፍረሱም ተቃዉሞዉም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ፎቶ ለማንሳት የሚሞክሩትን ካሜራና ሞባይል ስልክ በመንጠቅ በማስጠንቀቂያ ከአካባቢዉ እንዲርቁ ተደርገዋል፡፡