በጀርመን የሚገኘው የአብያተ-ክርስቲያናት ጉባኤ የጀርመን መንግስት ዋልድባን እንዲታደግ ጥሪ አቀረበ

ህዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአባያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የጀርመን የልማት ሚኒስትር ለሆኑት ለሚ/ር ዲሪክ ኔቢል በጻፉት ደብዳቤ ዋልድባ በአለም ላይ እጅግ ውድቅ የሆኑ ቅርሶችን የያዘና ለዘመናት ተጠብቆ የቆየ በመሆኑ፣ የጀርመን መንግስት ይህን ገዳም እንዲታደግ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቋል።

ለሚኒሰትሩ የቀረበው ጥያቄ በጀርመን ጋዜጦች ላይ ታትሞ ወጥቷል። የኢትዮጵያ መንግስት በዋልድባ ዙሪያ ላይ የሚያካሂደው የሸንኮራ ልማት፣ ለገዳሙ ህለውና ስጋት ነው በሚል ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል።

ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ፕሮጀክቱ ይቀጥል አይቀጥል የታወቀ ነገር የለም። አቡነ ጳውሎስ  በህይወት በነበሩበት ጊዜ ዋልድባን አልታደጉትም በሚል ከፍተኛ ትችት ይቀርብባቸው እንደነበር ይታወሳል።