መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአብዛኛው የኤርትራንና የሶማሊያን ዜጎች ከጣሊያን በመጫን ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ የነበረችው ጀልባ ላምፔዱሳ በሚባለው የጣሊያን ደሴት አካባቢ ስትደርስ በመስጠሙዋ በውስጧ ከተሳፈሩት መካከል ከ130 በላይ የሚሆኑት መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር አስታውቋል።
እስካሁን 150 ሰዎችን ለማትረፍ የተቻለ ሲሆን፣ የ130 ሰዎች አስከሬን ደግሞ በወደብ ሰራተኞች ተሰብስቧል።
ጀልባዋ 500 የሚሆኑ ሰዎችን ይዛ ጉዞ መጀመሩዋ ታውቋል። ከተረፉት 150 ሰዎች መካከል 3 ሴቶች ይገኙበታል። ከሟቾች መካከል ህጻናት ይገኙበታል።