በድሬዳዋ ከተማ የተነሳውን ግጭት ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ/ም ) በድሬዳዋ ቀበሌ 09 ትናንት ነሃሴ 20 በኦሮምያና በሶማሊ ተወላጆች መካከል የተነሳው ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ግጭቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። ግጭቱ የከተማውን ህዝብ የማይወክልና አንዳንድ ግለሰቦች ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቀሰቀሱት ግጭት መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የድሬዳዋ ከተማ የስልጣን ክፍፍል ሁኔታ በከተማው ለሚታየው ተደጋጋሚ ግጭት መንስኤ ሆኖ ቆይቷል።