በዲላ፣ ሱሉሉታና አዳማ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ተከሰተ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዲላ ከተማ በተፈጠረው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ነዋሪዎች ፣ቢጫ ጀሪካኖቻቸውን አሰልፈው ወንዝ እየወረዱ ለመቅዳት ተገደዋል። ከዚህ ቀደም በ15 ቀን አንድ ቀን ይገኝ የነበረው የቧንቧ ውሃ አሁን በወር አንድ ቀን ለማግኘት እየቸገረ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
በሱሉልታም እንዲሁ ውሃ ከጠፋ ወራት በመቆጠራቸው ህዝቡ የቆሸሸና የተበከለ ውሃ ለመጠቀም መገደዱን የአካባቢው ምንጮች በቪዲዮ አስደግፈው የላኩት መረጃ ያሳያል
በአዳማ የተለያዩ ቀበሌዎችም እንዲሁ ከፍተኘባ የሆነ የውሃ እጥረት ተከስቷል። ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ባጋጠማቸው የአፋር፣ ምስራቅ ሀረርጌ.፣የአማራና የትግራይ ጠረፋማ ከተሞች በከፍተኛ የውሃ ችግር ተጠቅተዋል።