በደብረ-ብርሀን በማጅራት ገትር በሽታ ሰዎች እየሞቱ ነው

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በበሽታው እስካሁን ከ4 በላይ ሰዎች ሞተዋል። 3 ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ተኝተዋል።

በአዲስ አበባ የማጅራት ገትር በሽታ ክትባት መጀመሩን መዘገባችን ይታወሳል።

የማጅራት ገትር ሕመም በተዋህሲን አማካይነት ተከስቶ የአንጎልን ህብለሰረሰር በተለይ ከራስ ቅል በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚያጠቃ ሕመም ነው፡፡

በባክቴሪያ አማካይነት የሚከሰተው ማጅራት ገትር በሽታ በወረርሽኝ መልክ የሚተላለፍ ፣ በምድር ወገብ አካባቢ በሚገኙ አገራት በ10 ዓመት አንድ ግዜ የሚከሰት ሲሆን በኢትዮጽያ በ8 ኣመት አንድ ጊዜ እንደሚከሰት ከአ/አ ጤና ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

በሽታው በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ አማካነት የሚመጣ ሲሆን ዋናው የበሽታ ምልክት የአንገት መቆልመም፣ ትኩሳት፣ብርሃንን ለማየት መቸገር በዋንናነት ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይ በሕጻናት ላይ አናታቸው አካባቢ የማበጥ፣የማቅለሽለሽ ፣ትኩሳት ፣አእምሮ መሳት፣የቅዥትና የመሳሰሉ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡