በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድረጉ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ በኮሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት ፊት ለፊት ባደረጉት ተቃውሞ፣ የኮሪያ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን እርዳታ እንዲያቆም፣ ለአገዛዙ በኢንፎርሜሽንና ደህንነት በኩል የሚሰጠውን ስልጠና እንዲያቆም ጠይቀዋል። አገዛዙ ከሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ እየገዛ በህዝብ ላይ እልቂት እየፈጸመ ነው ሲሉ ኢትዮጵያውያን አክለው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ሁላችንም ፈይሳ ሌሊሳ ነን፣ የኦሮሞ ፣ የአማራ ፣የኮንሶ፣ የጋምቤላ ደም ደማችን ነው በማለት የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።