መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አገሪቱ የሚታየው የስኳር እጥረት እልባት ባያገኝም፣ በደቡብ ክልል እጥረቱ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝቡ ለሻሂ የሚሆን ስኳር ማግኘት አለመቻሉን እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል ግን በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት የጥርነፋ ስልት የቡድን መሪ የሆኑ ነጋዴዎች፣ መንግስት የሚያከፋፍለውን ስኳር፣ እየጫኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እንደሚያሻግሩት ነዋሪዎች ይገልጻሉ። መሰረታዊ የሚባሉትን የዘይትና ስኳር አቅርቦቶችን መንግስት ራሱ በዘረጋው የማከፋፋያ መንገድ እየሸጠ መሆኑ ይታወቃል።