በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የታሰሩ ከ200 በላይ ሰዎች እስካሁን አልተፈቱም

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በቁጫ  ወረዳ  የተነሳውን  ህዝባዊ  ተቃውሞ ተከትሎ  ከአመት  በላይ  ለሆነ  ጊዜ  በአርባምንጭ  እስር  ቤት  ታስረው  የሚገኙት  ዜጎች ፣ ፍትህ አጥተው  አሁንም ስቃይ ላይ  መሆናቸውን  የአካባቢው ምንጮች  ገልጸዋል።

ባለፉት 3 ቀናት ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ 5 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ተቃውሞውን ለማዳፈን ሙከራ ቢያደርጉም፣ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ህዝቡ ጥያቄውን በድጋሜ በማንሳት አመጽ ሊቀሰቅስ ይችላል በማለት፣ ህዝቡን ያስተባብሩ ይሆናል ብለው የጠረጠሩዋቸውን ሰዎች ይዘው በማሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

ሰመጉን በአርባምንጭ እስር ቤት የሚገኙትን የቁጫ ተወላጆች ስም ዝርዝር ይፋ ማደረጉ ይታወሳል።