ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009)
በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ ወደ አጎራባች ዞኖች በመዛመት ላይ መሆኑ ስጋት እንዳሳደረበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድጋሚ ገለጸ።
በተለይ በኦሮሚያ ክልል ስር በሚገኙ የባሌ፣ ጉጂ፣ እና ቦረና ዞኖች በአዲስ መልክ የተከሰተው የድርቅ አደጋ በአካባቢው ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት አደጋ ውስጥ እንደከተቱ ድርጅቱ አስታውቋል።
ከደቡባዊ ምስራቅ የሃገሪቱ አካባቢዎች በተጨማሪ በደቡብ ክልል ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች የድርቅ አደጋ ያንዣበበባቸው ሲሆን፣ በአጠቃላይ 236 ቀበሌዎች በከፍተኛ የውሃ እጥረት ውስጥ መሆናቸው ታውቋል።
በመስከረም ወር መጣል የነበረበት ዝናብ በአግባቡ ባለመገኘቱ ሳቢያ ይኸው አዲስ የድርቅ አደጋ ሊከሰት መቻሉን የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።
ባለፉት ሁለት አመታት በድርቅ አደጋ ጉዳት ደርሶበት የቆየው የአፋር ክልል ዳግም የድርቅ አደጋ ያጋጠመው ሲሆን፣ በክልሉ በሚገኙ በርካታ ዞኖች አስደንጋጭ የሆነ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ድርጅቱ አሳስቧል።
በአካባቢው ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ተከትሎ ካለው የምግብና የውሃ እጥረት የኮሌራ በሽታን ጨምሮ ለሌሎች ተላላፊ በሽታዎች መከሰት ምክንያት ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል።
በቀጣዮቹ ሁለት ወራቶች ብቻ ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልግ ሲሆን ድርቁ እስከ ሚቀጥለው አመት ድረስ ዘላቂ እንደሚሆን ተተንብዮአል።
በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ሲካሄዱ የቆዩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች የዕርዳታ እህልን ለተረጂዎች ለማድረስ ሲደረግ በነበረው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮ መቆየቱን አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ይገልጻሉ።
በአሁኑ ወቅት 9.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ተጋልጠው የሚገኙ ሲሆን፣ በአዲስ መልክ የተከሰተው የድርቅ አደጋ የተረጂዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ ያደርጋል ተብሎ ተሰግቷል።
ካለፈው አመት ጀምሮ በኢትዮጵያ ተከስቶ የሚገኘው የድርቅ አደጋ በሃገሪቱ ታሪክ በ50 አመት ውስጥ ሲከሰት