ግንቦት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው መንግስት በከተማዋ ግንቦት19 ጠርቶት የነበረው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ በሰልፉ ለመገኘት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከከሸፈ በሁዋላ፣ በድጋሜ በማግስቱ ህዝቡ የስኳርና የዘይት ኩፖን ይዞ እንዲወጣ ጥሪ ቢደረግለትም ለመውጣት ፈቃደና ባለመሆኑ የተወሰኑትን በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁትን ሰዎች ብቻ በመያዝ በአሉን አክብሮአል። ዛሬ ግንቦት 24 ደግሞ ህዝቡ ነገ በሰልፍ ለኢህአዴግ ድጋፉን እንዲገልጽ ለማድረግ ካድሬዎቹ ቤት ለቤት በመዞር ህዝቡብ እያስፈራሩ ነው።