ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ ከ15 በላይ የፋይናንስና የማዘጋጃ ሰራተኞች በሙስና በሚል ተሰብስበው ታስረዋል።
እርምጃው የተወሰደው በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ነው። የድርጅተ ሰራተኞች እንደገለጹት በሙስና የተዘፈቁት ዋናዎቹ አመራሮች ሆነው እያለ እነሱን ወደ ሌሎች ቦታዎች በማዛወር፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ተራ ሰራተኞች ይዘው አስረዋል።
እስሩን ተከትሎ በሰራተኞች ዘንድ አለመረጋጋት መፈጠሩን ሰራተኞች ተናግረዋል። የከተማው ከንቲባና ዋና ዋና የድርጅቱ አባላት ከአካባቢው እርቀው ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዲመደቡ በማድረግ፣ በደሃ ሰራተኞች እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ለመሸንገል ሙከራ እያደረጉ ነው ሲሉ ሰራተኞች በሃዘን ገልጸዋል። ከሰአት በሁዋላ በደረሰን መረጃ ደግሞ የተያዙት ሰራተኞች ወደ ሃዋሳ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል።