ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ያንኮቪች መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን በተመለከተ ያወጣው አዲስ ህግ ያስቆጣቸው ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት ከፖሊሶች ጋር እየተጋጩ ነው።
መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን ለመገደብ ያወጣው አዲሱ ህግ በሌሎች የአውሮፓ አገራት ሳይቀር ተወግዟል።
ተቃዋሚዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ከመወርወራቸውም በተጨማሪ፣ መኪኖችን ሲያቃጥሉ ታይቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ያንኮቪች ድርጊቱ የዩክሬንን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
ግፊቱ የበዛባቸው ፕሬዚዳንት ያንኮቪች ከተቃዋሚዎች ጋር ለመነጋገር ሀሳብ አቅርበዋል።