የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት በአንዋር መስጊድ ድንገተኛ ተቃውሞ መደረጉን ተከትሎ ፖሊስ የጸጥታ ቁጥጥሩን በማጠናከር ፍተሻዎችን ሲያካሂድ ቢያረፍድም፣ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ግን ተቃውሞአቸውን በድምጽ ከማሰማት ያቆማቸው አልነበረም።
“ኮሚቴው ይፈታ፣ መንግስት የለም ወይ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል። መንግስት የኮሚቴው አባላትን ሞራል ለመስበር የተለያዩ የፈጠራ ዜናዎችን እያሰራጨ መሆኑን ድምጻችን ይሰማ ማስታወቁ ይታወቃል።55