መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዛንቢያ የስደተኞች ቢሮ በአገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ በመግባታቸው ክስ ከቀረበባቸውና የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ሃያ ስድስት የውጭ አገር ዜጎችን ወደየትውልድ አገራቸው መመለሱን አስታውቆ፣ ከእነዚህ መካከል 16ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ከኬንያ ጀምሮ ባሉት የመሸጋገሪያ አገራት ውስጥ አያሌ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስርቤትና በታጋቾች በደልና ስቃይ እየደረሰባቸው ሲሆን ፣ ኤንባሲዎች ዜጎቻቸውን ለመታደግ የሚያደርጉት ጥረት አለመኖሩ ሰቆቃቸውን አብዝቶታል። ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው የስራ ዋስትና ማጣት፣የኑሮ ውድነት፣የዴሞክራሲና የነጻነት እጦት ሰለባ በመሆናቸው ስደትን እንደ አማራጭ እንደወሰዱት አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ።