በዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ የተከሰሱት ታዋቂ ፖለቲከኞች በድጋሜ ተቀጠሩ

ታኀሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሽብረተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነጻ ያሰናበታቸው ታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች ሃብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም አብርሃም ሰለሞን ፣ አቃቢ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ነጻ ከተባሉትበት ከነሃሴ 14 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ።
ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ታህሳስ 29/2008 ዓ.ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኑ ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም ዳኛ ዳኜ መላኩ ‹‹የምንመረምረው ነገር አለ›› በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡