በዓለምአቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ቢያሽቆለቁልም በኢትዮጵያ አሁንም የዋጋ ማሻሻያ አልተደረገም

ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ዓለም የነዳጅ ዋጋ አሽቆልቁሏል። በኢራን ላይ የተጣለው የኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ መነሳቱን ተከትሎ የነዳጅ አቅርቦት ምርት መትረፍረፉን የምጣኔ ሃብት ጠበብቶች እየገለፁ ነው። በየቀኑ ከግማሽ ሚሊዮን በርሜል በላይ ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት የማቅረብ አቅሙ ያላት መሆኑን የኢራን ምክትል የነዳጅ ሚንስቴር የሆኑት ሮኬንዲ ጃቫዲ ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በአሁኑ ወቅት የአንድ በርሜል የነዳጅ ዘይት ዋጋ በአማካኝ 28 የአሜሪካን ዶላር ሆኖ ሳለ፣ በኢትዮጵያ ያለው ዋጋ ግን ቀድም ብሎ ሲሸጥበት በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል መደረጉ በህዝቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫናን ፈጥሯል።