በወረዳ አንድ የቤት ማፍረስ ዘመቻው ተጠናክሮ ቀጥሎአል

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ትናንት ቤታቸው የሚፈርስባቸው ዜጎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ በህዝቡ በኩል ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች እንዲሁም 2 ፖሊሶችና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪ ቢገደሉም፣ ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ወደ ጎን በማለት ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻውን ቀጥሎበታል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገ ሲሆን፣ ቤቶቹ ወደ ሚፈርሱባቸው አካባቢዎች መጠጋትም ሆነ ማለፍ አይቻልም። የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን ወጣቶች አፍሰው ወደ ዝዋይ መውሰዳቸውንም የአይን እማኞች ተናግረዋል። ባለፉት 3 አመታት ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች አካባቢያችንን አንለቅም በማለት አሁንም ድረስ ድንኳን ሰርተው የተቀመጡ አሉ።