በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀሌ ከተማ መሃከል ሊደረግ የነበረው ጫወታ በኮማንድ ፖስቱ ትእዛዝ ተቋረጠ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በትናንትናው እለት በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲግራት ከተማ በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀሌ ከተማ መሃከል ሊካሄድ የነበረው ጫወታ በደጋፊዎች መሃከል በተነሳ ረብሻ ተቋርጧል።
ጫወታው ዛሬ እንዲደገም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማኅበር ውሳኔ ቢያሳልፍም ኮማንድ ፖስቱ ጫወታው እንዳይካሄድ ማገዱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። በትናንትናው እለት በደጋፊዎች መሃከል በተነሳ ረብሻ ከመቋረጡ አስቀድሞ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 1ለ0 እየመራ ነበር።