በወልቂጤና በጎንደር አድማ አስተባብረዋል የተባሉ ወጣቶች እየታሰሩ ነው
(ኢሳት ዜና የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በጉራጌ ዞን ለሳምንት ተደርጎ የነበረውን የስራ ማቆም አድማ አስተባብረዋል የተባሉ ወጣቶች እየታደኑ በመያዝ ላይ መሆናቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች እና በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚሳተፉ ዜጎች ሰልፍ አስተባብራችሁዋል በሚል ምክንያት ታስረዋል። እንዲሁም ማደኛ የወጣባቸው መምህራን መኖራቸውንም ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በተመሳሳይ መንገድ ጎንደር ከተማ ትናንት የተጠናቀቀውን የስራ ማቆም አድማ መርተዋል የተባሉ ወጣቶች እየተፈጉ በመታሰር ላይ ናቸው። በከተማዋ የተሰማሩት ወታደሮች ወጣቶችን ወደ እስር ቤት መውሰዳቸውንና እስካሁን ድረስ እንዳልፈቷቸው ታውቋል።
በጎንደርና በጉራጌ ዞን የስራ ማቆም አድማው ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።