በኮንሶ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት 8 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው።

ሰዎቹ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና ዘመዶቻቸው ለፖሊስ አባላት ሄደው በሚያመለክቱበት ወቅት የእነሱ ጉዳይ ከባድ ነው ጠብቁ የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻልንም የሚሉት ሌሎች አባሎች፣ በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ይናገራሉ።

የዞኑን የፖለስ አዛዥ ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።