በኮሬ እና በጉጂ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት እንደገና በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከሃምሌ 2009 ዓም ጀምሮ በጉጂና በኮሬ ማህበረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት አንዴ ከፍ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለ ሲሆን፣ ሰሞኑን ደግሞ እንዳዲስ በማገርሸቱ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው። ሰሞኑን በተነሳው ግጭት ከሁለቱም ወገን 5 ሰዎች ሲገደሉ 11 ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወላይታ ክርስቲያን ሆስፒታልና ቡሌ ሆራ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።
በአስቸኳይ አዋጁ ስም የተሰማሩት የወታደራዊ እዙ አባላት በማረጋጋት ስም በአማሮ ወረዳ ፣ ደዳ ቡለኢቶ ቆሬና ጂጆላ አካባቢ አቶ አለማየሁ አፌቶ እና አቶ አበበ ዘቤና የተባሉ ሰዎችን ገድለዋል። ሶስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱ ዛሬም ድረስ በመቀጠሉ የጉዳቱ መጠን እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።