በኮሪያ በኢትዮጵያ ኢምባሲ የተጠራዉ የግንቦት 20 በአል ዝግጅት ተቃውሞ ገጠመው

ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ3 ቀናት በፊት በአምባሳደር ሽፈራዉ ጃርሶ የሚመራው ኢምባሲ ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት ደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ዉስጥ በሚገኘው ባለ 5 ኮከብ ሎቴ ሆቴል ያዘጋጀው ዝግጅት በአገሪቱ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንዳጋጠው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ኢምባሲው የሚስጥር ጥሪ ወረቀት መላኩንና እንግዳ ሆነው የተገኙት የህወሃት አባላት ብቻ መሆናቸውን የሚገለጹት ኢትዮጵያውያን፣ በግብዣው ላይ የተጠሩት የሌሎች አገሮች ዲፕሎማቶች ተቃውሞን እየተመለከቱ “ ይቅርታ” እያሉ መግባታቸውን ገልጸዋል።