በኮማንደ ፖስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ባንተወስን አበበ አሁንም አልተፈታም

በኮማንደ ፖስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ባንተወስን አበበ አሁንም አልተፈታም
(ኢሳት ዜና ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆነው ባንተ ወሰን አበበ ቀደም ብሎ በሽብር ወንጀል ተከሶ ኢህአዴግ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ከእስር ቤት የወጣ ቢሆንም፣ በሳምንታት ውስጥ እንደገና ተይዞ ታስሯል። ላለፉት 57 ቀናት በእስር ቤት የሚገኘው ባንተወሰን ፍርድ ቤት አለመቅረቡንና በከፍተኛ ችግር ላይ መሆኑን ወንድሙ ፈቃዱ አበበ ተናግሯል። ባንተ ወሰን በእስር ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈጸመበት፣ ላለፉት 57 ቀናት ሰውነቱን ታጥቦ እንደማያውቅ፣ ቤተሰብ ምግብ እያመላለሰለት መሆኑን እንዲሁም የኩላሊት ህመሙ ቢነሳበትም ህክምና እንዳያገኝ መደረጉን ፈቃዱ ተናግሯል። የጋሞ ጎፋ ዞን የጸጥታና አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ቤታ አንጀሎ በባንተ ወሰን ላይ ስቃይ የሚፈጽምበት ግለሰብ መሆኑን ገልጿል።
የጋሞ ጎፋ ዞን የጸጥታና አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ቤታ አንጀሎ በበኩላቸው የባንተወሰን ጉዳይ በኮማንድ ፖስቱ የተያዘ መሆኑንና እነሱም እንዲፈታ ቢጠይቁም ከኮማንድ ፖስቱ መልስ ማጣታቸውን ተናግረዋል።