ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2008)
የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶችን በክልል የሚሰጡ አውቶቡሶች በአዲስ አበባ የተቀሰቀሰውን የስራ ማቆም ተቃውሞውን ሰኞ እንደተቀላቀሉት ታውቋል።
በአሰላ፣ ባሌ፣ እና ሮቤ ከተሞች የተጀመረው የትራስፖርት ማቆም አድማ ተከትሎም በየከተሞቹ የትራንስፖርት እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ ታክሲዎች አገልግሎታቸውን እንዲጀምሩ ጥሪን ቢያቀርቡም የታክሲ ማቆም አድማው ሰኞ ምሽትም መስተዋሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።