በኬንያ ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ እየመሩ ነው

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዚዳንት ልጅ የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ ተቀናቃኛቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋን በሰፊ ልዩነት እየመሩ ነው። እስካሁን በተደረገው ቆጠራ ሚስተር ኬንያታ 53 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው 42 በመቶ አግኝተዋል።

የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ሀላፊ እንደተናገሩት ውጤቱ ጊዜያዊ በመሆኑ፣ ህዝቡ በትእግስት እንዲጠብቅ መክረዋል።

እስካሁን አንድ ሶስተኛው ድምጽ የተቆጠረ ሲሆን ኡሁሩ ኬንያታ በሰፊ ድምጽ እየመሩ ነው።

በ2007-2008  የተደረገውን የምርጫ ውዝግብ ተከትሎ  ከ 1000 ያላነሱ ኬንያውያን መገደላቸው ይታወሳል።

የኬንያ ባለስልጣናትና ሚዲያዎች  ህዝቡ የምርጫውን ውጤት በሰለጠነ መንገድ እንዲከታተል መክረዋል። ታዋቂው ዘ ደይ ሊ ኔሽን ጋዜጣ ” ምርጫው ኬንያ የሰለጠነች አገር ሆና እንድትቀጥል ወይም እንዳትቀጥል ያደርጋታል” ብሎአል።

ከአጠቃላዩ ድምጽ ውስጥ 51 በመቶ ያገኘ የአገሪቱ ቀጣይ ፕሬዚዳንት ይሆናል። የኬንያ ምርጫ ያለምንም ደም መፋሰስ በሰላም ከተጠናቀቀ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ነጻ ምርጫ ተብሎ ይመዘገባል።