ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንደፈጸመው በተገመተው በዚህ ጥቃት 48 ሰዎች ተገድለዋል። የቱሪስት መዳረሻ በሆነቸው በላሙ ደሴት በደረሰው ጥቃት ሆቴሎችና መኪኖችም ተቃጥለዋል።
ፖሊሶች ከታጣቂዎች ጋር ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ ታጠቂዎች ወደ ጫካ ገብተው ማምለጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ የፖሊስና የደህንነት ተጠሪያቸውን በማስጠራት በቀጣይ ስለሚወስዱት እርምጃ መክረዋል። አልሸባብ በኬንያ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸመ ነው። ኬንያ ጦሩዋን ወደ ሶማሊያ አስገብታ ከአልሸባብ ጋር እየተፋለመች መሆኑ ይታወቃል።
በአለም ዋንጫ የተዘጋጀ ስፖርት ዘገባ ከዜናው በሁዋላ ይኖረናል