ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብተዋል ያላቸውን 27 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችንና ወደ ደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት ሰጥተን እናሻግራችኋለን ያሏቸውን ሕገወጥ ስደተኛ አዘዋዋሪ ደላሎችን ፖሊስ ይዞ ኢምቡ ፍርድ ቤት አቀረበ።
ከስደተኞቹ ውስጥ ሶስቱ የ13 የ14 እና 15 ዓመት ታዳጊዎች ሲሆኑ በደላሎች ዓማካኝነት ካለምንም ሕጋዊ ፈቃድ ድንበር ጥሰው በመግባታቸው ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ በማለት ውሳኔ አሳልፏል። በውሳኔውም መሰረት ሶስቱ ታዳጊዎች ካሳቸው ተነስቶ በፍጥነት ወደ ሀገራቸው እንዲመልሱና ቀሪዎቹ የ15 ሽህ የኬኒያ ሽልንግ መቀጮ ወይም የ9 ወራት እስራት ተበይኖባቸዋል። የቅጣት ክፍያውን ወይም የእስራት ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ አገራቸው እንዲላኩ መፈረዱን ዘስታርስ ዘግቧል።