በካናዳ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ አንድ ሴትን ሲገል 13 ሰዎች ቆሰሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በካናዳ ሕዝብ በሚበዛበት አካባቢ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ አንድ ሴትን ሲገል 13 ማቁሰሉ ተገለጸ።

የግለሰቡ ጥቃት ያነጣጠረው በሁለት ምግብ ቤቶች ላይ መሆኑ ደግሞ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ግለሰቡ በከፈተው ተኩስ ከቆሰሉት መካከል ሕጻናት እንደሚገኙበትም የተገለጸ ሲሆን ሕይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሴትም መኖሯ ታውቋል።

የ29 አመቱን ተጠርጣሪ ሞቶ መገኘቱንና ከዛ በፊት ግን ከፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲያደርግ እንደነበርም ተገልጿል።

የአካባቢው ፖሊስ ተጠርጣሪው አደጋውን ሊያደርስ የቻለበትን ምክንያትና ምናልባትም ጥቃቱ አሸባሪዎች የሰነዘሩት ይሁን አይሁን በማጣራት ላይ መሆኑን ሲ ኤን ኤን በዘገባው አመልክቷል።