ጳጉሜ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የንግድ እንቅስቃሴዎች ቆመዋል። የንግድ መደብሮች ተዘግተዋል፤ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አቁመዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች የስራ ማቆም አድማውን በጣሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ሻሸመኔ፣ አሰላ፣ ነቀምት፣ ባሌ ሮቤ ፣ ጊምቢ፣ ዶዶላ፣ ቆቦ፣ ዳዳር እና ሌሎችም በርካታ ከተሞች አድማውን ተግባራዊ እያደረጉ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ነጋዴዎች ስራቸውን እንዲጀምሩ የተለያዩ እርምጃዎችን ቢወስዱም አልተሰካላቸውም።
የስራ ማቆም አድማው የፈጠረውን ጫና ተከትሎ በግብርና ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እየታዬ መሆኑን ከሚደርሱን የገባያ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል።