በኦሮምያ ዋና ከተማ የውሃ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከማሃል ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ አካባቢዎች ውሃ ካጡ ረጅም ጊዜ አስቆጥረዋል።

ውሃ ጀሪካን በጋሪ ላይ ጭኖ መሄድ ወይም ለውሃ ወረፋ ረጃጅም ሰልፎችን መጠበቅ የእለት ተእለት ክስተት መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

በተመሳሳይም በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ የሚታየው የውሃ ችግር ሊቀንስ አልቻለም።

ኦሮምያን እመራለሁ የሚለው ኦህዴድም ሆነ ትግራይን የሚያስተዳድረው ህዋሃት በቅርቡ  በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማፍሰስ የልደት በአላቸውን ማክበራቸው ይታወቃል፡፡

በኦሮምያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ተማሪዎች በውሃ እጥረት ትምህርት እስከማቋራጥ መድረሳቸውን መዘገባችን ይታወቃል።