በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ በርካታ ዜጎች የዶ/ር አብይን መመረጥ ተከትሎ ደስታቸውን ወደ ጎዳና በመውጣት ገልጸዋል።

በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ በርካታ ዜጎች የዶ/ር አብይን መመረጥ ተከትሎ ደስታቸውን ወደ ጎዳና በመውጣት ገልጸዋል።
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) በቦረናና ጉጂ ዞኖች ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የደስታ ስሜቱን ሲገልጽ አምሽቷል። ዛሬም እንዲሁ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ደስታውን ሲገልጽ ውሎአል። ህዝቡ “ወያኔ ቻው ቻው” የሚል መፈክር ያሰማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በምስራቅ ሃረርጌም እንዲሁ ህዝቡ ዛሬ ጠዋት ወደ አደባባይ በመውጣት፣ መልካም ምኞቱን ሲገልጽ ውሎአል። “ዶ/ር አብይ ቃል የገባውን በተግባር ማሳየት አለበት” የሚል መልዕክት ሲተላለፍ እንደነበር የተመለከተ ሲሆን፣በተለይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቅድሚያ እንዲነሳ ማድረግ እንደሚገባው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።