በኦሮምያ በተለያዩ ቀበሌዎች በተደረጉት ስብሰባዎች የቀበሌ አመራሮች ተቃውሞአቸውን ገለጹ

ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ  አንድ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው “ ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል አጀንዳ ለ5 ተከታታይ ቀናት በተደረገው ስብሰባ  ላይ የቀበሌ አመራሮች ግምገማው ትክክል ያልሆነና የህዝቡን ብሶት ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብለዋል።

እናንተ ህዝባችንን ትገላላችሁ፣ እኛ ደግሞ አንድ ሰው እስከሚቀር ፣ ህዝባችን ጥያቄውን መጠየቁን አያቆምም። ጥልቅ ተሃድሶ የሚባል ከሆነ ዋናውን ችግር ትታችሁ ትንንሽ ጉዳይ ላይ ማተኮራችሁ ትክክል አይደለም። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተሳቦ ህዝባችንን ለመከራ ተጋልጦ ነው ያለውንና በዚህ አካሄድ ተቃውሞው መቀጠሉ አይቀርም “ ብለዋል። ስብሰባውን የመሩት ካድሬዎች በቀበሌ አመራሮች ያልተጠበቀ መልስ ግራ ተጋብተው ታይተዋል። የቀበሌ አመራሮች ስብሰባ በመጠናቀቁ፣ ስብሰባው ወደ ህዝቡ በቅርቡ ይወርዳል ተብሎአል።

በሌላ በኩል ባለፈው ቅዳሜ  በኦሮሞና በሶማሊድንበር አካባቢ በሚኖሩ በሁለቱ ብሄር ተወላጆች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ሰው መሞቱን ዘጋቢያችን ገልጿል። በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውንና ንብረትም መውደሙ ታውቋል። ግጭቱ ለረጅም ጊዜ የቆየ ቢሆንም፣ በስልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች ግጭቱ ሲበርድ እንደገና  በተመቻቸው ጊዜ በማስነሳት ለፖለቲካ ፍላጎታቸው እንደሚያውሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።