በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ለመጨፍለቅ መንግስት አስፈላጊውን የሃይል እርምጃ እንደሚወስድ ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 17, 2008)

ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኖ ያለውን የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ለማስቆም መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ሃሙስ በድጋሚ ገለጠ።

የመንግስት ባለስልጣናት የተጀመረውን የሃይል እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቢልጹም፣ በክልሉ ተቃውሞው ዳግም በመዛመት ላይ መሆኑን የተለያዩ አካላት አስታውቀዋል።

ተቃውሞው ዳግም ማገርሸቱን ተከትሎም የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከተቃውሞው ጀርባ የውጭና የውስጥ አካላት አሉ ሲሉ የገለጻቸውን አካላት በስም ከመግለጽ የተቆጠቡ ሲሆን፣ መንግስት ድርጊቱን ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከቀናት በፊት ተመሳሳይ ማሳሰቢያን ሰጥተው የነበረ ሲሆን ተቃውሞው ከማሳሰቢያው በኋላም መቀጠሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።