በኦማር ሀሰን አልበሽር መንግስት ላይ የተደረገው የመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ ከሸፈ።

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በሱዳኑን የመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ ሊያደርጉ የነበሩ የቀድሞው የ አገሪቱ የደህንነት ሀላፊ ሳላህ ጎሽ እና  ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢቢሲ ዘገበ።

የ ዓይን ምስክሮች እንደተናገሩት ሀሙስ ማርፈጃውን    ታንኮችና ታጣቂዎችን የጫኑ የጦር ተሽከርካሪዎች የካርቱምን ጎዳና አጨናንቀዋት ውለዋል።

ሱዳናውያን እያሻቀበ የመጣውን የኑሮ ውድነት በመቃወምና አስተዳደራዊ ለውጥ በመፈለግ በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን የዜና አውታሩ አስታውሷል።

ኦማር ሀሰን አልበሽር እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ 1989 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ላለፉት 23 ዓመታት ሱዳንን በፕሬዚዳንትነት ሲመያስተዳድሩ ቆይተዋል።

የሱዳን ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አህመድ ቢላል ኡስማን ከመፈንቅለ-መንግስቱ ሙከራ ጋር በተያያዘ እስካሁን 13 ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን የደህንነት ሹሞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

“ዓላማቸው ህጋዊውን መንግስት በማፍረስ  የአገሪቱን ሰላም ማናጋት ነበር ያሉት ሚኒስትሩ፤ሆኖም ድርጊታቸውን ከመፈጸማቸው በፊት መንግስታቸው  ደርሶ እንዳስቆማቸው ተናግረዋል።

መፈንቅለ-መንግስቱን መርተዋል የተባሉት ሚስተር ሳላህ ጎሽ የአልበሽር የቅርብ ወዳጅ ከመሆናቸውም በላይ እስከ 2009 ዓመተ ምህረት ድረስ የሱዳን የደህንነት ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide