ኢሳት (ሃምሌ 13 ፥ 2008)
በእነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መዝገብ በጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ተከሳሽ የነበሩት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካሳይ ላይ አቃቤ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ በሰውና በማስረጃ ማስረዳት በመቻሉ የ14ኛው ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ መተላለፉን የደረሰን ዜና ያመለክታል።
አቃቤ ህግ በጸረ-ሽብርተኝነቱ አዋጅ የከሰሳቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ 141 መከላከያ ምስክሮችን አስመዝገው እንደነበር የታወቀ ሲሆን፣ በተከሳሾች በኩል የተመዘገበው ጭብጥ ግን የፈጸሙት ተግባር ወንጀል ነው ወይስ አይደለም በሚል እንዲመሰክሩ በመሆኑና በአንድ ተግባር ወንጀል መሆን አለመሆኑን በህግ እንጂ በምስክር ስለማይረጋገጥ የምስክሮቹ መስማት አግባብነት ስለሌለው መታለፉ ተገልጿል።
ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለሃምሌ 22 ቀን 2008 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱም ተመልክቷል።
እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ኤርትራ ድንበር በማቋረጥ አርበኞች ግንቦት 7ትን ሊቀላቀሉ ሲያመሩ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ እንደቀረበባቸው የሚታወስ ነው።