በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ለወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ድጋፋቸውን ገለጹ የሚፈጸመውን  ግድያም አወገዙ

ሐምሌ  ፳፰ ( ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ቤተ እስረኤላውያን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄን ደግፈው፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። በኦሮምያ የሚፈጸመውን ግድያ አውግዘዋል። የታሰሩት ሁሉ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ወደ ኪዳነምረት ቤተክርስቲያን በማምራት ገዢው ፓርቲ የሚጠቀምበትን ሰንደቅ አላማ በማውረድ ኮከብ የሌለውን ሰንደቃላማ ሰቅለዋል። ድርጊቱን በተመለከተ ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆነው አቶ ማስተዋል ጥላሁን ድርጊቱን የፈጸሙት የቤተ ክርስቲያኑዋ አስተዳዳሪዎች ከዚህ ቀደም የቀረበላቸውን ጥያቄ መመለስ ባለመቻላቸው ነው ይላል።

ኢትዮጵያውያኑ  ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።