በእስራኤል ከ16ሺ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010) እስራኤል ወደ ሀገራቸው ልትመልሳቸው የነበሩ ከ16ሺ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ መወሰኗን አስታወቀች።

ለደህንነታቸው ሰግተውና ከሃገራቸው ሸሽተው በእስራኤል ጥገኝነት ጠይቀው የሚገኙ  ስደተኞች የኢኮኖሚ ስደተኞች ናቸው በሚል ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖ እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እንዳሉት ስደተኞቹን ወደ ሌላ ምዕራባውያን ሀገራት ለማስፈር እንደተወሰነ ገልጸዋል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ኤርትራውያን መሆናቸው የሚነገረው አፍሪካውያኑ ስደተኞች በግብጽ አድርገው ረጅም በረሀን አቋርጠው እስራኤል የገቡ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል።