(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2011) በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ከእነዚሁ አስቸኳይ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው መካከል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ናቸው ።
ለዚሁ እርዳታ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልገም ተገልጿል።
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሰታት ድርጅት እና ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተወካዮች ጋር ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛል።
በዚሁ ምክክርም በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
ኮሚሽኑ እንደገለጸው አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው 8 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች ውስጥም 8 ሚሊየን ሰዎች የቀጥታ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።
ከነዚሁ መካከልም እጅግ አስቸኳይ በሆነ ሁኔታ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው 4.4 ሚሊዮን ኢጥዮፕያዊያን ወሽጥ 6 መቶ ሺህ የሚሆኑት ክ 5 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት መሆናቸው ታወቋል።
አስቸኳይ እርዳታ ፈላጊዎቹ በኦሮሚያ ክልል 46 በመቶ፣ ሶማሌ ክልል 22 በመቶ፣ አማራ ክልል 12 በመቶ፣ ደቡብ ክልል 10 በመቶ እንዲሁም ትግራይ እና አፋር ክልሎች ደግሞ እያንዳንዳቸው 4 በመቶ ድርሻን እንደሚይዙ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቋል።
ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ከእነዚሁ አስቸኳይ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው መካከል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ናቸው ።
ይሕ አሀዝ ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ ቀርበው ከ 90 በመቶ በላይ ተፈናቃዮች ወደ የቦታቸው ተመልሰዋል ከሚለው ሪፖርታቸው ጋር የሚጋጭ ሆኗል።
ለአስቸኳይ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ በአጠቃላይ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልገም ተገልጿል።
ለምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ ከሚያስፈልገው ገንዘብም የኢትዮጵያ መንግስት 60 በመቶውን ይሸፍናል ተብሏል።
ቀሪውን 40 በመቶ ደግሞ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ለጋሽ ድርጅቶች ለመሰብሰብ መታቀዱ ነው የተገለጸው።
የኢትዮጵያ መንግስት ለአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ባለፈው ዓመት 342 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መድቧል።
ለጋሽ ድርጅቶች ደግሞ 595 ሚሊየን ዶላር አስተዋጽኦ ማድረጋቸውኝ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል።