ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2013 በነበረው ጊዜ ከፖሊዮ ነጻ አገር ተብላ የተወደሰች ቢሆንም፣ ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ በሽታው እንደገና መታየቱን ዩኒሴፍ አስታውቋል።
ባለፈው አመት 10 የፖሊዮ ተጠቂዎች መታየታቸውን የገለጸው ዩኒሴፍ፣ የበሽታው እንደገና መከሰት ለአገሪቱ ፣ ለቤተሰቦችና ለህጻናቱ እጅግ አደገኛ ክስተት ነው ብሎአል።
ኢትዮጵያ በሽታውን ለመከላከል ተጨማሪ 2 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሰጣት ዩኒሴፍ አክሎ ገልጿል። በሽታው በ በኬንያና በሶማሊያ መታየቱንም የድርጅቱ ሪፖርት ያመለክታል።