በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል
(ኢሳት ዜና የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በአገሪቱ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ ደረጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የተለያዩ የአምራች እንዱስትሪ ባለቤቶች ሲናገሩ ሲናገሩ ቢቆዩም፣ ችግሩ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጅ እየቀነሰ አልሄደም። በአሁኑ ሰዓት የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚጠበቀው ወረፋ ከአመት በላይ መሆኑን የሚናገሩት ባለሀብቶች፣ ያም ሆኖ በቂ ዶላር ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል ይላሉ።
በጥቁር ገበያ የዶላርና የዩሮ ምንዛሬ በህጋዊ መንገድ ከባንክ ከሚመነዘርበት ከፍተኛ ጭማሪ ያለው በመሆኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የጀመሩ ግለሰቦች ዶላር ለማግኘት የጥቁር ገበያውን እንደ ጥሩ አማራጭ አድርገው ወስደውታል።
በአገሪቱ የሚታዬው የቱሪስት ፍሰት መቀነስ፣ የውጭ ኢንቨስትመንት መቀነስና የወጪ ንግዱ መቀዛቀዝ የዶላር እጥረቱን ከአባባሱት ምክንያቶች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።
በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ወደ አገራቸው የሚልኩትን የውጭ ገንዘብ፣ በህጋዊ መንገዶች እንዳይልኩ የተጠናከረ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ናቸው።