ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ የሳምባ ምች በሽታ የመጀመሪያው ገዳይ በሽታ የነበረ ሲሆን፣ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ኤች አይ ቪ ኤድስ አንደኛ የአእምሮ ጭንቀት ደግሞ የሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኤ አይ ቪ ኤድስ በኢትዮጵያ እየቀነሰ መምጣቱ ቢነገርም፣ በሽታው አሁንም ቀዳሚ ገዳይ በሽታ ተብሎአል። የአእምሮ ጭንቀት ሁለተኛ ገዳይ በሽታ መሆኑ ቢታወቅም፣ መንስኤው ምን እንደሆነ በደረሰን መረጃ አልተገለጸም።
ኢትዮጵያውያንን በብዛት ከሚገድሉት መካከል ኤድስ ፣ የአዕምሮ ጭንቀት ፣ የሳምባ ምች በሽታ ፣ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ፣ የደም ተቕማጥ ፣ ወባ ፣ የልብ ድካም ፣ ትርፍ አንጀት፣ ማናጃይት ፣ እና የመኪና አደጋዎች ከ1 እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
በተመላላሽ እና በአስተኝቶ ማከም ክፍል ከታዩት ህሙማን ውስጥ አብዛኞቹ በሳምባ ምች እና በወባ የተጠቁ ናቸው፡፡