ግንቦት ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤጀንሲ ጽህፈት ቤት ይዞ በወጣው የወርሃዊ የዋጋ ዝርዝር ጥናት መሰረት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በምግብ ነክና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎች መታየታቸውን አስታውቋል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ 12 ነጥብ 2 ከመቶ የነበረው የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ወደ 12 ነጥብ 3 ከመቶ ከፍ ብሏል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች በበኩላቸው በሚያዚያ ወር ከነበሩበት 4 ነጥብ 6 ከመቶ ወደ 4 ነጥብ 7 ከመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።