ታኅሣሥስ ፫ (ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መመሪያውን ተከትለው ሁሉም የባንክና የኢንሹራንስ ድርጅቶች ማስታወቂያ በማውጣት ደንበኞቻቸውን እያሰናበቱ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር FIS/01/2016 ባወጣው መመሪያ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 5.1 እና 5.2 መሰረት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ አገርዜግነት ያላቸው የባንክ ወይም ኢንሹራንስ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች ከህዳር 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 60 ቀናት ውስጥ ዋናውን የአክሲዮን የምስክር ወረቀታቸውን እንዲሁም ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ የአክሲዎናቸውን ዋጋ እንዲወስዱ አስጠንቅቋል።
ገዢው ፓርቲ ከ250 ሺ ብር በላይ አካውንታቸው ላይ ገንዘብ የተገኘባቸው ዜጎች ማንነት አሳውቁ በማለት ግዴታ በማጣሉ እና የደንበኞችን ሚስጥር ያለአግባብ የሀገሪቱን ህግ እና ደንብ በጣሰ ሁኔታ በደብዳቤ እና በውስጥ መመሪያ እያዘዘ በስራችን ላይ እቅፋት እየፈጠረብን ነው በማለት የባንክ እና ኢንሹራንስ ስራ አስኪያጆች ሲያማርሩ ቆይተዋል።