ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009)
በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ በኢሳት ላይ የተመሰረተውን ክስ የአሌክሳንድሪያ ከተማ ፍ/ቤት ውድቅ አደረገ።
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በገንዘብ ድጋፍ የሚያደርላቸው ግለሰቦችና አካላት በአሜሪካ ፍ/ቤቶች በኢትዮጵያውያን ተቋማት ግለሰቦች ላይ የመሰረቱት ክስ የቀጠለ ቢሆንም፣ እንደተለመደው በዚሁ ሳምንት ውድቅ መደረጉ ያበሳጫቸው አንድ ዲፕሎማት ነኝ ያሉ በአደባባ ዘለፋ ሲያካሄዱ ተደምጠዋል።
በኢሳት፣ በኢሳት የቀድሞ ማኔጂንግ ዳይረክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ እና በኢሳት ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ላይ የተመሰረተው ክስ በቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ከተማ ፍ/ቤት በሳምንቱ መጀመሪያ ውድቅ አድርጎታል። ኢሳትን ወክለው የተከራከሩት ጠበቆች ሚስተር ኸርማን ሶውየርና ዶር/ ፍጹም አቻምየለም እንደነበሩ መረዳት ተችሏል።
በዋሽንግተን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ “ኢምባሲዬ ተደፈረ” በሚል በዋሽንግተን ዲሲ አክቲቪስቶች ላይ የመሰረተው ክስ ውድቅ እንደተደረግም ይታወሳል። በአንጻሩ የኢምባሲው የጥበቃ ሃላፊ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከአሜሪካ መባረራቸውም አይዘነጋም። የትግራይ ክልል ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ እንዲሁም የቀድሞ የኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ጥቃትና ወከባ ድርሶብናል በሚል የመሰረቱትም ክስ የአሜሪካ ፍ/ቤቶች ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል። የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት በቀጠሯቸው ወቅት ከኢትዮጵያ ለምስክርነት የመጡ ቢሆንም ጉዳዩ ውድቅ ሲደረግ ተመልሰው ሄደዋል።
ከክሱ ውድቅ መሆን ጋር በተያያዘ አንደሆነ በተገመተ መልኩ ኣንድ ዲፕሎማት ነግን ያሉ ግለሰብ ከችህሎት ዉጭ አንድ ዘለፋ ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
እኝሁ አቶ ሃጎስ ስዩም የተባሉ ግለሰብ “ወያኔ ጀግና ነው፣ ሃገራችሁ አትገቡም” ሲሉም ተደምጠዋል።