በኢትዮጵያ አፋጣኝ ዴሞክራሲያዊና ኤኮኖሚያዊ የለውጥ ተሃድሶ እንዲደረግ የአስቸኳይ አዋጁ እንዲነሳ ሲል የአሜሪካ ኤምባሲ ጠየቀ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የዶ/ር ዓብይ አህመድን መመረጥ አስመልክቶ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪክ ኤምባሲ በመግለጫው እንዳለው መንግስታቸው የአዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር መሾም በበጎ ጎኑ እንደሚያየውና ከዶ/ር አብይና የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ የጋራ ግንኙነት እንደሚቀጥል ገልጿል።
በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መሰረት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በሰላም ስልጣናቸውን አስረክበዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ስልጥናቸውን ሲለቁ በገቡት ቃል መሰረት የፖለቲካ ተሃድሶ እና ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር እንዲደረግ የገቡት የተስፋ ቃል ገቢራዊ ይሁን ብሎአል።
የኢትዮጵያ መንግስት በአፋጣኝ ዴሞክራሲያዊና ኤኮኖሚያዊ የለውጥ ተሃድሶ እንዲያደረግ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲነሳ የአሜሪካ መንግስት ይጠይቃል ሲል የኢምባሲው መግለጫ አመልክቷል።