በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ፍልሰት እና በተፈጥሮ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተመድ አስታወቀ።
( ኢሳት ዜና መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአገር ውስጥ ግጭቶች ምክንያት የከመኖሪያ ቀያቸው የሚፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እየጨመረ ነው ። በያዝነው ዓመት አጋማሽበደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ቁጥራቸው ከ818 ሽህ በላይ ሰላማዊ ዜጎች በማፈናቀል ከፍተኛው ቁጥርይዘዋል። በሶማሊያ ክልል በጅጅጋና አካባቢው ለሁለት ቀናት በቀጠለ የእርስበእርስ ግጭት 141 ሽህ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
ይህን ተከትሎበዘንድሮው ዓመት የሰብዓዊ ረድኤት ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምርዋል። ባለፈው ተመሳሳይ ዓመት 2017 እ.ኤ.አ. በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ቁጥራቸው ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ሰላማዊ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን ያታወሳል።በአብዛሃኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች የተሻለ ምርት ያገኛሉ ተብሎ ቢጠበቅም፤ በተወሰኑ የአፋር፣ አማራ፣ ትግራይ እና ሶማሊያ ክልል ከመደበኛዝናብ በታች ዝቅተኛ ዝናብ ይጥላል ተብሎ ይጠበቃል። ይህን ተከትሎ ቁጥራቸው ከ7.9 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ ዕርዳታያስፈልጋቸዋል ሲል ሪሊፍ ዌብ ዘግቧል።